የፓትሪያሊኩ መልእክት
የአረማውነት ሥራ እንዲቆም በተደጋጋሚ ጊዜያት ሞክሬ አልተሳካም!
በምስጢር ተቀድቶ የወጣው የቪድዮ መልእክታቸው ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ታፍኛለሁ አሉ።
«ስለ ትግራይ ስናገር ድምጼ ይታፍፈናል። በትግራይ ጭካኔ የተሞላበት የአረመናዊነት ድርጊት እንዲቆም ብዙ ጊዜ ሞክሬ አልተሳካም። ሚያዝያ 7 ያደረኩት ኢንተርቪው ታግዷል። ስቃወም ድምጼ ይታፈናል። የአለም ሚዲያ እየተናገራው እኛ እንዳንናገር ታፍነናል።»
በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ብዙ ግፍ ተሠርቷል። በትግራይ ላይ የተደረገው ግን ይበልጣል በማለት ተናግረዋል።
ለዓለም መንግሥታት፣ ለዓለም አብያተ ክርስቲያናት የተለየ የድጋፍ ጥያቄ ጠይቀዋል።
"የአለም ሚዲያ እየተናገረው እኛ እንዳንናገር ታፍነላል"
"ባሁን ጊዜ በሀገራችን በኢትዮጵያ በተለይም ደግሞ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው አረመኔያዊነት፣ የአረማውነት ስራ እንዲቆም በተደጋጋሚ ጊዜያት ሞክሬ አልተሳካም ፤ ምክንያቱም ፍቃድ አልተሰጠም። እናገራለሁ ይመልሱታል፣ እናገራለሁ ይመልሱታል፤ ይኸው እስካሁን ጊዜ ምንም አይነት ፍቃድ አልተገኘም።
እናም ሁላችሁም ወገኖቻችን ማወቅ ያለባችሁ፣ እዚህ ያለውን ችግር፣ የኔን ችግር የማውቀው እኔ ነኝ።"
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
==========••
Self comment
==========••
የመተከል አማራ መገደሉ ሳይበቃ በግሬደር እንደቆሻሻ ተዝቆ ተቀብሯል። በወለጋ እናቶችና ህፃናት ታርደዋል። በማይካድራ ሺዎች በአሳቃቂ መንገድ ታርደዋል። በጌዴኦ፣ በኮንሶ፣ በሻሸመኔ ምድር በደም ጨቅይታለች። በአጣዬ ከተማ ወድሟል። ጳጳሱ በነዚህ ከተሞች እና አካባቢዎች ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃትን አላወገዙም።
በትህነግ እብሪት ምክንያት የትግራይ ህዝብ ለስቃይ መዳረጉ ያሳዝናል። ነገር ግን የሆነው ሁሉ የሆነው 21 አመት የጠበቀውን የሰሜን እዝ በተኛበት ከኋላው በክህደት ካራ ታርዶ የገባንበት ጦርነት ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ